ሰበታ ከተማን ለማሰልጠን ስምንት አሰልጣኞች ተፋጠዋል

ሰበታ ከተማዎች በያዝነው ሳምንት መጨረሻ አዲሱን የክለቡ አሰልጣኝ ይፋ የሚያደርጉ ሲሆን ለዚህም ሹመት ስምንት አሰልጣኞች ታጭተዋል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በድንገት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሳልፈው ከሰጡ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ባሳለፍነው ሳምንት ዓርብ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥተው የነበሩት ሰበታ ከተማዎች በዛሬው ዕለት የቅጥሩን ሒደት አጠናቀው ስምንት አሰልጣኞችን የለዩ ሲሆን ቀጣዩ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ማን ይሆናል የሚለው ጉዳይ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ይፋ እንደሚሆን በተለይ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት ለመረከብ እየተወዳደሩ ያሉ ስምንት አሰልጣኞች የሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ የነበሩት ፀጋዬ ኪዳነማርያም፣ ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተሰረዘው የውድድር አጋማሽ የተለያዩት አዲሴ ካሣ፣ በቅርቡ ስሑል ሽረን ሲመሩ የነበሩት ሳምሶን አየለ፣ ሰበታ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመለሱት ክፍሌ ቦልተና፣ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ውላተው የተጠናቀቀው ጳውሎስ ጌታቸው፣ የቀድሞው የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለረጅም ዓመታት በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ዘሪሁን ሸንገታ እና የሰበታ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ የነበሩት ብርሀን ደበሌ የሰበታ ከተማ ቀጣዩ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን የተፋጠጡ አሰልጣኞች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!