የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በኢትዮጵያዊው ዳኛ ይመራል

ሞሮኮ ላይ የሚካሄደውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ ይመራዋል፡፡

ግንቦት ላይ መጠናቀቅ የነበረባቸው የ2019/20 ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድሮች በኮቪድ 19 ከተቋረጡ ከረጅም ጊዜያትን አስቆጥረዋል፡፡ ውድድሮቹ ከሰሞኑ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዳግም ሲመለሱ በሞሮኮ ራባት በሚገኘው ፕሪንስ ማውላይ አብደላ ስታዲየም የፊታችን ማክሰኞ ምሽት 4፡00 የግብፁ ፒራሚድ ከጊኒው ሆሮያ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ እንዲመራው በካፍ ተመርጧል፡፡ ረዳቶቹ ደግሞ የኬንያው ጊግበርት ቺሮይት እና የሱዳኑ መሐመድ አብደላ ኢብራሂም ሆነዋል።

በዓምላክ ይህን ውድድር ለመምራት ከሰሞኑ በግብፅ የአቅም ግንባታ እና የተለያዩ ስልጠናዎችን ከሌሎች አፍሪካዊያን ዳኞች ጋር ሲወስድ ቆይቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!