ሀዋሳ ከተማ ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

ሀዋሳ ከተማዎች በቀጣዩ ሳምንት የ2013 ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ፡፡

የቀድሞው ተጫዋቻቸውን አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን ከሰባት ወራት በፊት በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ሀዋሳ ከተማዎች ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ዝግጅት ልምምዳቸውን የፊታችን ረቡዕ ጥቅምት 11 የክለቡ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች፣ የቡድኑ አጠቃላይ አባላት የኮቪድ 19 ምርመራን በተጨማሪነት ደግሞ የሜዲካል ህክምናን አድርገው ወደ ካምፕ ከገቡ በኃላ ከጥቅምት 14 ቀን 2013 ማለዳ ጀምሮ የቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በክረምቱ የዝውውር መስኮት አምስት አዳዲስ ተጫዋቾች በማድረግ ያስፈረሙቶ ሀዋሳዎች ወደ ሰበታ ባመራው አጥቂው እስራኤል እሸቱ ምትክ እንዲሁም ተጨማሪ ወሳኝ የተባለ ዝውውር በጥቂትት ቀናት ይፈፅማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!