ስሑል ሽረ አራተኛ ተጫዋቹን አስፈረመ

ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ ዘግየት ብለው የገቡት ስሑል ሽረዎች የመስመር ተጫዋች አስፈርመዋል፡፡

ለክለቡ ፊርማውን ያኖረ አራተኛ ተጫዋች የሆነው የቀኝ መስመር አማካይ እና አጥቂው ሱራፌል ዳንኤል ነው። ድሬዳዋ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ቁልፍ ሚና ከነበራተው ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ይህ ፈጣን ተጫዋች ክለቡን ከለቀቀ በኃላ በ2011 ወደ አዳማ ከተማ ተጉዞ የተጫወተ ሲሆን ዓምና ደግሞ በሀድያ ሆሳዕና በመጫወት ካሳለፈ በኃላ ቀጣይ ማረፊያውን በአንድ ዓመት የውል ዕድሜ ስሑል ሽረን አድርጓል፡፡

በአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀም የሚመራው ስሑል ሽረ ከዚህ በፊት አሌክስ ተሰማ፣ ደሳለኝ ደባሽ እና ዘካሪያስ ፍቅሬን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!