ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዳማ ከተማ የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዘመ

አዳማ ከተማ የተከላይዋ ወይንሸት ፀጋዬን ኮንትራት አራዝሟል፡፡
ወሳኝ የሚባሉ ተጫዋቾቹን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ ከሰሞኑ የሰጠው አዳማ ከተማ ቀሪዎቹን ተጫዋቾችን የማቆየት እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ማስፈረሙ የገባ ሲሆን ወይንሸት ፀጋዬን አምስተኛ ውል ያራዘመች ተጫዋች በማድረግ ለሁለት ተጨማሪ አመት አስፈርሟል፡፡ በኢትዮጵያ ቡና ተጫውታ ያለፈችው እና ከደደቢት ጋር ወርቃማ ጊዜያትን በማሳለፍ 2011 ወደ አዳማ አምርታ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በክለቡ ጥሩ ግልጋሎት ስትሰጥ የነበረችው ተጫዋቿ ከደደቢት ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳች ሲሆን በመጀመሪያ ዓመት የአዳማ ቆይታዋም በተመሳሳይ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!