ስሑል ሽረዎች የ2013 ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በዚህ ሳምንት ይጀምራሉ።
የእስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረሙት ሽረዎች ላለፉት ወራት ለተጫዋቾቹ ደመወዝ ካለመክፈል ጋር በተገናኘ ጥያቄ ሲነሳበት የቆየ ሲሆን ክለቡ ይህን ችግር ለመቅረፍ እየሰራም ይገኛል፡፡በተጠናከረ መልኩ ችግሮቹንም ቀርፎ ወደ ውድድር ለመቅረብ እየሰሩ ያሉ ሲሆን ለፕሪምየር ሊጉ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በዚህ ሳምንት ይጀምራሉ፡፡
በዛሬው ዕለት ለሁሉም ተጫዋቾች ጥሪን አቅርቦ ተጫዋቾች አሰልጣኞች እና የቡድኑ አጠቃላይ አባላት የኮቪድ 19 ምርመራን ያደረጉ ሲሆን ከሁለት ቀናት በኃላ ደግሞ በይፋ ልምምዳቸውን ይጀምራሉ፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!