ወልዋሎዎች የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀቁ

ባለፈው ሳምንት አራት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

የመጀመርያው ፈራሚ የመስመር ተከላካዩ ሽመልስ ተገኝ ነው። ከሙገር ወደ መከላከያ በማምራት ለረጅም ዓመታት በጦሩ ቆይታ ያደረገው ሽመልስ ከአንድ ዓመት የከፍተኛ ሊግ ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመልሰውን ዝውውር ሲያደርግ ባለፈው ሳምንት ለቢጫዎቹ ከፈረመው ዓወት ገብረሚካኤል ጋር ለቦታው ቋሚ ተሰላፊነት ይፎካከራል።

ሌላው ፈራሚ አብዱልባሲጥ ከማል ነው። ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ወደ ደደቢት በማምራት በውድድር ዓመቱ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በማሳየት ከመሀል ሜዳ አየተነሳ አራት ግቦች ያስቆጠረው ታታሪው አማካይ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኃላ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!