ስሑል ሽረ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ስሑል ሽረዎች የሁለት ቁልፍ ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዘመዋል።

ዲዲዬ ለብሪ ካራዘሙት መካከል ነው። ከሦስት ዓመት በፊት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ፈርሞ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው እና በእግርኳስ ሕይወቱ ለአስራ ሁለት የተለያዩ ክለቦች ተዘዋውሮ የተጫወተው ፈጣኑ አማካይ ከዚ በፊት ለሴፋክስ፣ ኤስፔራንስ እና አል ሜሪክ ተጫውቷል። ጅማ አባ ጅፋርን ለቆ ወደ ሽረ ካመራ በኋላ ባለፈው የውድድር ዓመት ጥሩ ጊዜ ካሳለፉ የክለቡ ተጫዋቾች አንዱ ነው።

ሁለተኛ ከክለቡ ጋር ለመቆየት ውሉን ያራዘመው ሁለገቡ አብዱልለጢፍ መሐመድ ነው። ባለፈው የውድድር ዓመት በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ከክለቡ ጋር ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው ይህ ጋናዊ ውድድሩ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች በመሆን ዘልቋል። ከኮቶኮ አካዳሚ የተገኘው ይህ ጋናዊ ፉትሮ ኪንግስ ፣ ሞናና ፣ አሻንቲ ጎልድ እና ሲዳማ ቡና ከተጫወተባቸው ክለቦች መካከል ናቸው።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!