ቀደም ብሎ ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ተስማምቶ የነበረው ታሪክ ጌትነት ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል።
ከደደቢት የረጅም ጊዜ ቆይታ በኃላ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ በክለቡ የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው ታሪክ ባለፈው የውድድር ዓመት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ አድርጓል። ከአቤር ኦቮኖ ጋር እየተፈራረቀ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው ይህ ግብጠባቂ ምንተስኖት አሎ እና ወንድወሰን አሸናፊ ላጡት ስሑል ሽረዎች ጥሩ ፊርማ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።
አሌክስ ተሰማን በማስፈረም የዝውውር መስኮቱ እንቅስቃሴ የጀመሩት ስሑል ሽረዎች እስካሁን ድረስ ደሳለኝ ደባሽ ፣ ዘካርያስ ፍቅሬ ፣ ሱራፌል ዳንኤል እና ታሪክ ጌትነትን አስፈርመዋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!