ወላይታ ድቻ ተጫዋቾቹን ጠርቷል

ወላይታ ድቻዎች የ2013 የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በቀጣዩ ሳምንት ይጀምራሉ፡፡

በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ የሚመራው ወላይታ ድቻ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የነባሮቹን ውል ያደሰ ሲሆን የ2013 የቅድመ ውድድር ዝግጅቱንም ለመጀመር ቀን ቆርጧል። ሰኞ ጥቅምት 16 ለተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና ለቡድኑ አጠቃላይ አባላት የኮቪድ 19 ምርመራን ካደረገ በኃላ ውጤቱን መሠረት በማድረግ በሦስት ቀናት ውስጥ ቅድመ ውድድር ዝግጅት እንደሚጀምር ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!