የከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ታወቀ

የ2013 የከፍተኛ ሊግ ውድድር በታኅሣሥ ወር ይጀመራል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን በሦስት ምድቦች ተከፍሎ እንደተለመደው በሠላሳ ስድስት ክለቦች መካከል ይከናወናል፡፡ ውድድሩ ዘንድሮ በኮቪድ 19 ምክንያት በተመረጡ ሜዳዎች ላይ ብቻ የሚደረግ ሲሆን ክለቦችም ለዚህ ውድድር ዝግጅት እንዲያደርጉ እና ከጥቅምት 16 እስከ ህዳር 26 ድረስ ምዝገባ እንዲፈፅሙ በደብዳቤ ገልጿል። አሁን ደግሞ ውድድሩ የሚጀመርበትን ቀን ፌዴሬሽኑ ማሳወቁን የውድድር ዳይሬክቶሬቱ አቶ ከበደ ወርቁ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት የ2013 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ታኅሣሥ 10 እንዲጀመር መወሰኑን የገለፁልን ሲሆን ቀደም ብሎ የዕጣ ማውጣት እና ከክለቦች ጋርም ውይይቶች እንደሚኖሩ ገልፀውልናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!