ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዕለተ ዕሁድ ጀምሮ ተጫዋቾቹ ለዝግጅት እንዲሰበሰቡ ጥሪ አድርጓል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ያጣውን ዋንጫ ዳግም በእጁ ለማስገባት በማለም ጀርመናዊው የቀድሞ ካይዘር ቺፍስ አሰልጣኝ ኤርነስት ሜደንዶርፕን ትናንት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ያስተዋወቀው ክለቡ አሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ ጀምሮ ስለ ክለቡ አጠቃላይ ገለፃ እና ማብራሪያ እንዲሁም አብረዋቸው የሚዘልቁትን ተጫዋቾች ሲያስተዋውቅ ሰንብቷል። ነገ ደግሞ የቡድኑ አባላት ወደ ካምፕ ገብተው የኮቪድ 19 እና አጠቃላይ ሜዲካል ምርመራን እንደሚያርጉ ሰምተናል፡፡ በምርመራውም ውጤቱ በሁለት ቀናት ከታወቀ በኃላ የፊታችን ረቡዕ መቀመጫቸውን ክለቡ በቢሾፍቱ ባስገነባው የይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ አካዳሚ ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!