አዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

አዳማ ከተማ ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝ ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡

ለ2013 የውድድር ዓመት የቀድሞው ረዳት አሰልጣኙን አስቻለው ኃይለሚካኤልን በይፋ የሾመው አዳማ ከተማ ከአሰልጣኙ ደጉ ዱባሞ ሌላ ረዳት አሰልጣኝ በቡድኑ ውስጥ ጨምሯል፡፡ አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ ደግሞ ለቦታው ተመራጭ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ክለቦች በርከት ያሉ ጊዜያቶችን ያሳለፉት አሰልጣኙ ቡራዩ ከተማን ከለቀቁ በኃላ ሻሸመኔ ከተማን ይዘው ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ጠንካራ ተፎካካሪ በማድረግ የዘለቁ ሲሆን በክለቡ ዘንድሮ ተጨማሪ ኮንትራት እንደሚሰጣቸው ቢጠበቅም ወደ አዳማ ከተማ ማምራታቸው ታውቋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!