የካ ክፍለከተማዎች ለ2013 የውድድር ዘመን የበርካታ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅሙ የወሳኝ ተጫዋቾችንም ውል አድሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ የሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ በቅርቡ የአሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸውን ውል ያደሰ ሲሆን የ2013 የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅታቸውን በቅርቡ ለመጀመር ተዘጋጅተዋል። ለዚህም ውላቸው የተጠናቀቁ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ኮንትራት ለተጨማሪ ዓመት ሲያራዝም አንድ ጋናዊ አጥቂን ጨምሮ አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾች በአዲስ መልክ ወደ ስብስቡ በይፋ በማስፈረም ቀላቅሏል፡፡
ውል ያራዘሙ ተጫዋቾች – ዮሐንስ አድማሴ (ተከላካይ)፣ ንጉሥ ጌታሁን (ተከላካይ)፣ ተስፋዬ ሀይሶ (ተከላካይ)፣ ብሩክ መስፍን (ተከላካይ)፣ መሐሪ ዮሴፍ (ተከላካይ)፣ ግርማ ዓለሙ (አማካይ)፣ አንተነህ ከተማ (አማካይ)፣ ሚኪያስ አምሀ (አማካይ)፣ ዳንኤል ለታ (አማካይ)
ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች – ወርቅነህ ዲባባ (ግብ ጠባቂ ከቂርቆስ)፣ አሕመድ ሙሐመድ (ግብ ጠባቂ ከባሌ ሮቤ)፣ ሚሊዮን ሰለሞን (ግብ ጠባቂ ከካፋ ቡና)፣ ሄኖክ ከሎ (ተከላካይ ከአዲስ ከተማ)፣ ፍጹም ጉዱ (ተከላካይ ከቂርቆስ)፣ አማረ ሰጡ (ተከላካይ ከኢትዮጵያ ቡና)፣ እዮብ ተሾመ (አማካይ ከደብረማርቆስ)፣ ኪሩቤል ይጥና (የመስመር አጥቂ ከአዲስ ከተማ)፣ ተስፋዬ በቀለ (የመስመር አጥቂ ከወልቂጤ)፣ መሐመድ ናስር (የመስመር አጥቂ ከስልጤ ወራቤ)፣ ዮናስ ሀብቴ (የመስመር አጥቂ ከአራዳ ክፍለከተማ)፣ ክብረአብ ማቱሳላ (አጥቂ ከሶሎዳ ዓድዋ) ፣ ማቲያስ ሹመታ (አጥቂ ከወልዲያ) እና የጋና ዜግነት ያለው አጥቂው ቤንጃሚን ኦዶም
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!