ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የበርካታ ነባሮችን ውል አራዘመ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ተወዳዳሪ የሆነው ጋሞ ጨንቻ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም፣ የአራት ነባሮችን ውል በማራዘም እና ወጣቶችን በማሳደግ ዓመቱን ጀምሯል፡፡

በ2007 የተመሠረተው እና ከኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ካደገ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ሲወዳደር የቆየው ጋሞ ጨንቻ ለዘንድሮ ተሳትፎው በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ እየተመራ ለአዲሱ የውድድር ዘመን እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡ አሰልጣኙ ለ2013 የውድድር ዓመት የጤና ጥበቃ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መመሪያን ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት ሁሉን በማሟላት በሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ነግረውናል፡፡

ለክለቡ የፈረሙ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች – አስጨናቂ ፀጋዬ (አማካይ ከሀምበሪቾ ዱራሜ)፣ ሲሳይ ማሞ (የመሐል ተከላካይ ከሶዶ ከተማ) እና ዘላለም በየነ (አጥቂ ከሶዶ ከተማ)

ከተስፋ ቡድን ያደጉ አራት ታዳጊዎች – አሸናፊ ወልደማሪያም (አጥቂ)፣ ምንተስኖት መስፍን (አማካይ)፣ ንጋቱ ፀሐዬ (ተከላካይ) እና ብሩክ ሳህሌ

ውል ያራዘሙ አስር ተጫዋቾች – ደሣለኝ አሎ፣ ታደለ ፈለቀደ በለጠ በቀለ፣ መኮንን መና፣ በኃይሉ በርዛ፣ ወንድወሰን ኤርሚያስ፣ ምንተስኖት በትሩ፣ እንዳልካቸው መስፍን፣ በድሉ ሰለሞን እና መሠረት ማላቆ

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!