ስሑል ሽረ ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ስሑል ሽረ የ29 ዓመቱን ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ አስፈረመ፡፡

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለመጀመር ለተጫዋቾቻቸው የኮቪድ 19 ምርመራን ያደረጉት ስሑል ሽረዎች የዩጋንዳ ዜግነት ያለው ግብ ጠባቂ ብሪያን ብዌቴን በአንድ ዓመት ውል የክለቡ አራተኛ አዲስ ፈራሚ አድርገው ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል። የ29 አመቱ ይህ ግብ ጠባቂ በሀገሩ ክለብ ቢድኮ ቡል እና ዩአርኤ እንዲሁም በዲሪ ኮንጎው ቡካቩ ዳዋ የተጫወተ ሲሆን ባለፈው የወድድር ዓመት ወደ ዛምቢያው ሙፉሊራ ወንደረርስ ቢያመራም ከግማሽ ዓመት ቆይታ በኋላ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ተከትሎ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።

“ዚጊ” ቡዌቴ ሽረን ለቆ ወደ ሰበታ ያመራው ምንተስኖት አሎን ቦታ እንደሚሸፍን ይጠበቃል።

*ማስታወሻ – የውጪ ዜጋ ግብ ጠባቂዎችን ማስፈረም እንደማይቻል የቀረበው ረቂቅ ደንብ እስካሁን አለመፅደቁ ይታወቃል። በተጨማሪም ክለቦች የውጪ ተጫዋቾችን ከአንድ ዓመት የውል ርዝመት በላይ ማስፈረም እንደማይችሉ መገለፁ ይታወሳል። LINK

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!