ከፍተኛ ሊግ ፡ አማራ ውሃ ስራ ባህርዳርን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ አንድ ጨዋታ አስተናግዶ አማራ ውሃ ስራ ባህርዳር ከተማን ማሸነፍ ችሏል፡፡ በሁለቱ የባህርዳር ክለቦች መካከል የሚደረገው ጨዋታ የአማራ ውሃ ስራ ተጫዋቾች በኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በመጠቃታቸው ምክንያት ለዛሬ ተላልፎ የነበረ ሲሆን ዛሬ በ9፡00 በተደረገው ጨዋታ አማራ ውሃ ስራ ባህርዳርን በፍቅረማርያም እና ፋንታሁን ግቦች 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ የባህርዳርን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ተዘራ ጌታቸው በፍፁም ቅጣት ምት ነው፡፡ ድሉ አማራ ውሃ ስራን በደረጃ ሰንጠረዡ 3 ደረጃዎችን እንዲያሻሽል አድርጎታል፡፡

የሊጉ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው እሁድ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሎ ይውላል፡፡

ምድብ ሀ

እሁድ 20/06/2008

ሁሉም ጨዋታዎች 09፡00 ላይ ይደረጋሉ

መቐለ ከተማ ከ አክሱም ከተማ (መቐለ)

ባህርዳር ከተማ ከ ወልድያ (ባህርዳር)

ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን አማራ ውሃ ስራ (ደብረብርሃን)

ወሎ ኮምቦልቻ ከ ወልዋሎ (ኮምቦልቻ)

ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ከ ኢትዮጵያ መድን (አበበ ቢቂላ)

ሙገር ሲሚንቶ ከ ቡራዩ ከተማ (አሰላ)

ሱሉልታ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ (ሱሉልታ)

ፋሲል ከተማ ከ አአ ፖሊስ (ጎንደር)

HL A

 

ምድብ ለ

እሁድ 20/06/2008

ከዚህ በታች ያሉ ጨዋታዎች በሙሉ 09፡00 ላይ ይደረጋሉ

ሻሸመኔ ከተማ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ (ሻሸመኔ)

ጅማ ከተማ ከ ወራቤ ከተማ (ጅማ)

ደቡብ ፖሊስ ከ አርሲ ነገሌ (ሀዋሳ)

ነቀምት ከተማ ከ ነገሌ ቦረና (ነቀምት)

ጅንካ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ (ጅንካ)

ባቱ ከተማ ከ ጅማ አባ ቡና (ባቱ)

ናሽናል ሴሜንት ከ ፌዴራል ፖሊስ (ድሬዳዋ)

07፡00 ፡ አዲስ አበባ ከተማ ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አበበ ቢቂላ)

HL B

ያጋሩ