ሽመልስ በቀለ ብሔራዊ ቡድኑን የሚቀላቀልበት ቀን ታውቋል

የዋልያዎቹ አንበል እና ቁልፍ ተጫዋች የሆነው ሽመልስ በቀለ ዋልያዎቹን የሚቀላቀልበት ቀን ታውቋል።

በቀጣይ ወር መጀመርያ ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ምድብ ማጣርያ ጨዋታዋን ከኒጀር ጋር የምታደርገው ኢትዮጵያ ዋሳኙ ተጫዋቿን የፊታችን አርብ የምታገኝ ይሆናል። ሽመልስ አርብ ጠዋት አዲስ አበባ በመግባት ወድያውኑ ከሰዓት አልያም ቅዳሜ ከቡድኑ ጋር በመቀላቀል ልምምድ እንደሚጀምር ለማወቅ ችለናል። የአማካዩ ስብስቡን በመቀላቀል በቡድኑ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎም ይጠበቃል።

ለግብፁ ክለብ ምስር ለል ማቃሳ እየተጫወተ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ከኮሮና ቫይረስ መቋረጥ በኃላ በተጀመረው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ጥሩ ብቃቱን በማሳየት ለቡድኑ መሻሻል ጥሩ አስተዋፅኦ እያደርገ ሲሆን ዋልያዎቹ ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጉት የነጥብ ጨዋታ አይቮሪኮስት ላይ የማሸነፍያ ጎል ከማስቆጠሩ ባሻገር ድንቅ እንቅስቃሴ ማድረጉ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ