የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሁለቱ የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ በስብስቡ የሚገኙ ተጫዋቾች ቁጥር ወደ 26 ዝቅ መደረጉ ይፋ ሆኗል።
ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኒጀር ብሄራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው ጨዋታ አዲሱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ41 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከመስከረም 25 ጀምሮ በካፍ ልህቀት ማዕከል ዝግጅት እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ከዛምቢያ ጋር ካደረጋቸው ጨዋታዎች በኋላ በዝግጅት ላይ ከነበሩ 36 ተጫዋቾች መካከል 10 ተጫዋቾች መቀነሳቸው ይፋ ተደርጓል።
በቀን ዘገባችን ላይ ባለፈው ጨዋታዎት ተሳትፎ እንዳላደረጉ የገለፅናቸው ሰዒድ ሀብታሙ፣ ደስታ ደሙ፣ ፍፁም ዓለሙ እና አቤል ያለው ከተቀሱት መካከል ሲሆኑ አቤል ማሞ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ሚኪያስ መኮንን፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና ኃይለሚካኤል አደፍርስ እና አዲስ ግደይ ሌሎች ተቀናሾች ናቸው።
በስብስቡ ውስጥ የቀሩ 26 ተጫዋቾች
(ሽመልስ ዓርብ ቡድኑን እንደሚቀላቀል የሚጠበቅ ሲሆን ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾች ከኒጀሩ ጉዞ በፊት እንደሚቀነሱ ይጠበቃል)
ግብ ጠባቂዎች
ተክለማሪያም ሻንቆ፣ ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ ምንተስኖት አሎ፣ ጀማል ጣሰው
ተከላካዮች
ወንድሜነህ ደረጀ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ያሬድ ባየህ፣ አስቻለው ታመነ፣ ሱሌይማን ሰሚድ፣ ረመዳን የሱፍ፣ መሳይ ጳውሎስ
አማካዮች
አማኑኤል ዮሐንስ፣ ታፈሰ ሰለሞን፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ሀይደር ሸረፋ፣ ጋዲሳ መብራቴ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ከነዓን ማርክነህ፣ በረከት ደስታ፣ መስዑድ መሐመድ፣ ይሁን እንደሻው፣ ሽመክት ጉግሳ
አጥቂዎች
ሙጂብ ቃሲም፣ ጌታነህ ከበደ፣ አቡበከር ናስር፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!