Soccer Ethiopia

ሀዋሳ ከተማ የመስመር አጥቂ አስፈረመ

Share

የመስመር አጥቂው ኤፍሬም አሻሞ በይፋ ለሀዋሳ ከተማ ፊርማውን አኖረ፡፡

በሙገር ሲሚንቶ የእግር ኳስ ሕይወቱን ከጀመረ በኃላ ለሐረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክ፣ ደደቢት፣ ወልዋሎ እና ያለፈውን ዓመት ለመቐለ 70 እንደርታ በመጫወት ያሳለፈው ባለ ልምዱ ፈጣን የመስመር አጥቂ ኤፍሬም ለትውልድ ከተማው ሀዋሳ በይፋ ፈርሟል፡፡ በዚህም ታላቅ ወንድሙ ጌታሁን አሻሞ እና ታናሹ ብርሀኑ አሻሞ የለበሱትን የሀዋሳ መለያ በዘንድሮ የውድድር ዓመት የሚለብስ ይሆናል።

ሀዋሳ ከተማዎች የወሳኝ ተጫዋቾቹን ብሩክ በየነ እና ሄኖክ ድልቢን ጨምሮ የበርካታ ነባር ተጫዋቾችን ውል ያራዘሙ ሲሆን ሶሆሆ ሜንሳ፣ ዳግም ተፈራ፣ ምኞት ደበበ፣ ዘነበ ከድር፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ጋብርኤል አህመድን ማስፈረማቸው ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top