አዲሱ የኒጀር አሰልጣኝ ለኢትዮጵያው ጨዋታ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ኒጀር ስብስቧን ይፋ አድርጋለች።

በአፍሪካ ዋንጫ የሞድቦ ማጣርያ የመጀመርያዎቹ ሁለት ጨዋታዎቿን በአይቮሪኮስት እና ማዳጋስካር የተሸነፈችው ኒጀር የምድቡ ቀጣዮ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎችን ኖቬምበር 13 በሜዳዋ፤ ኖቬምበር 17 ደግሞ በባህር ዳር ከኢትዮጵያ ጋር ትጫወታለች። ለነዚህ ጨዋታዎች ስብስቧን ይፋ ያደረገችው ኒጀር አብዛኞቹ ተጫዋቾች ከሃገር ውስጥ ሊግ የተመረጡት ሲሆን በዴንማርኩ HB Køge የሚጫወተውን አማካዩ አደባዮር ዛካሪን አለመምረጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል። በፈረንሳዩ ሎርዮ የሚጫወተው ሄርቬ ሊቦሂይ እና በጊኒው ሆሮያ የሚጫወተው አጥቂው መሐመድ ዋንኮዬ በስብስቡ የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው።

ስብስብ

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!