ተስፈኛው አማካይ ቃልአብ ጋሻው ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል።
በዝውውር መስኮቱ ዘግይተው በመግባት በርካታ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉት ስሑል ሽረዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ሻሸመኔ ከተማ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው አማካዩ ቃልአብ ጋሻውን አስፈርመዋል። ከሼር ኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን የተገኘው እና ለባቱ ከተማ፣ ቡራዩ ከተማ እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዓመት በሻሸመኔ ከተማ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች በርካታ አማካዮች ላጡት ሽረዎች ጥሩ ፊርማ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም እየተመሩ ዝግጅት ለመጀመር ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ ያቀረቡት ስሑል ሽረዎች በቀጣይ ቀናት በሽረ እንዳሥላሰ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!