ድሬዳዋ ከተማ ሦስት ወጣቶችን ወደ ዋናው ቡድን ቀላቅሏል

ድሬዳዋ ከተማ ሦስት ወጣት ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን ማካተቱን ይፋ አድርጓል፡፡
ትናንት ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዝግጅት ለተጫዋቾቹ ጥሪ ያቀረበው ድሬዳዋ ከተማ በክረምቱ በርከት ያሉ ዝውውሮችን ፈፅሞ የነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሰ ሲሆን አሁን ደግሞ ሦስት ወጣቶችን ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ማሳደጉን አስታውቋል፡፡ ግብ ጠባቂው አብዩ ካሳዬ እና የመስመር አጥቂው ሲያን ሱልጣን ከድሬዳዋ ከተማ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ያደጉ ሲሆን የመሐል ተከላካዩ ሚኪያስ ካሣሁን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ስብስቡን የተቀላቀሉ ወጣቶች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!