ድሬዳዋ ከተማ የቀድሞ ተጫዋቹን አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ የቀድሞ የመሐል ተከላካዩን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ለድሬዳዋ ከተማ በ2011 የተጫወተው ፍቃዱ ደነቀ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከላካይ የባንክን መፍረስ ተከትሎ በመቐለ እና ድሬዳዋ የአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ደግሞ በወልዋሎ ሲጫወት ቆይቶ ለአሰልጣኝ ፍሰሀ ጡዑመልሳኑ ክለብ በአንድ ዓመት ውል ፈርሟል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!