ከፍተኛ ሊግ | ጌዲኦ ዲላ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ጌዲኦ ዲላ በዛሬው ዕለት አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ላይ ተወዳዳሪ የሆነው ጌዲኦ ዲላ ከአስራ አምስት ቀናት በፊት አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን አውጥቶ የነበረ ሲሆን በርካታ አሰልጣኞች ካወዳደረ በኃላ አሰልጣኝ ኢዮብ ማለን ለአንድ አመት ቀጥሯል፡፡ የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ የነበሩት ኢዮብ ማለ በ2011 ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃንን ከብሔራዊ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊጉ በማሳደግ እንዲሁም ክለቡን በተሰረዘው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊግ በመምራት አሳልፈው ዛሬ ዲላን ተረክበዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ