ኒጀሮች የአቋም መለክያ ጨዋታ አደረጉ

ቀጣይ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ኒጀር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ስታደርግ ከቀናት በኃላም ሁለት ጨዋታዎች ለማድረግ ቀጠሮ ይዛለች።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በደርሶ መልስ ኢትዮጵያን የምትገጥመው ኒጀር በትናንትናው ዕለት ያደረገችው የአቋም መለክያ ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቃለች። በሜዳቸው ማሊን ያስተናገዱት ኒጀሮች በጨዋታው ሰሰላሳ አራተኛው ደቂቃ ባሳኩ ባስቆጠራት ግብ በተጋጣሚያቸውን ቢመሩም ብዙም ሳይቆዩ ከአስር ደቂቃ በኃላ በዳሬንኩም አማካኝነት ባስቆጠሯት ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ኒጀሮች ከሁለት ቀን በኃላ ኖቬምበር አንድ እና ኖቬምበር አራት ከሞሮኮ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል። በአሰልጣኝ ሀሊልሆድዚች የሚመሩት ሞሮኮዎች በደካማው ምድብ ማውሪታንያ፣ ማዕከላዊ አፍሪካና ብሩንዲን አስከትለው ምድባቸውን በአራት ነጥብ መምራት ይገኛሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!