የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወቅታዊ መረጃዎች

በኅዳር ወር መጀመርያ ከኒጀር ጋር የምድቡን ሦስተኛ እና አራተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርገት ዋልያዎቹ አሁን የሚገኙበትን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲህ አጠናቅረናል።

* ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት በሚጫወትበት የግብፅ ሊግ ውድድር የነበረበት በመሆኑ ቡድንን ሳይቀላቀል የቆየው ሽመልስ በቀለ ትናንት አመሻሽ ላይ አዲስ አበባ መግባቱ ተረጋግጧል። ሆኖም ዛሬ ልምምድ ይጀምራል ቢባልም ሐሙስ በግብፅ ሊግ ጨዋታ የነበረው በመሆኑ ዛሬ እረፍት አድርጎ ነገ ጠዋት ልምምድ ሊጀምር እንደሚችል ይጠበቃል።

* በጉዳት ከሁለት ቀን በፊት ልምምድ ያቋረጠው ሙጂብ ቃሲም ዛሬ ለብቻው ተነጥሎ ቀለል ያለ ልምምድ እንደጀመረ ሰምተናል።

* ሌላው ጉዳት ያስተናገደው አማንኤል ዮሐንስ ከጉዳቱ አገግሞ እርሱም እንደ ሙጂብ ለብቻው ቀለል ያለ ልምምድ ሲሰራ ተስተውሏል።

* ሌላኛው ጉዳት አስተናግዶ በሁለቱ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ያልተሰለፈው አቡበከር ናስር ወደተሟላ ልምምድ ከቡድኑ ስብስብ ጋር ተካቶ መሥራት መጀመሩ ለብሔራዊ ቡድኑ መልካም ዜና ሆኗል።

*የአቋም መለኪያ ጨዋታን በተመለከተ ጥቅምት 27 አርብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሱዳን ጋር እንደሚጫወት ተረጋግጧል።

* 27 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዱን ያከናወነ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ የመጨረሻ 23 ተመራጭ ተጫዋቾቹን የሚያሳውቅ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!