ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ@

በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠረው አቃቂ ቃሊቲ ወደ ዝውውሩን በመቀላቀል ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሦስት ነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡

በቅርቡ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን አውጥቶ በርካታ አሰልጣኞችን ካወዳደረ በኃላ ለረጅም አመታት በሴቶች እግር ኳስ ላይ በመስራት የሚታወቀውን አሰልጣኝ ብዙአየው ዋዳን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው አቃቂ ቃሊቲ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ ጠንክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ረጅም ጊዜ በአማካይ ስፍራ ስትጫወት የነበረችው ዙለይካ ጁሀድን ጨምሮ ገነት ሰጠ (ተከላካይ ከመከላከያ)፣ አበዛሽ ሜጊሶ (ተከላካይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሒሩት ደምሴ (የመስመር አጥቂ ከቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ትዕግስት ሽኩር (አማካይ ከልደታ ክፍለከተማ እና ትደግ ፍሰሀ (አጥቂ ከመቐለ 70 እንደርታ) ወደ ክለቡ የቀላቀለ ሲሆን በክለቡ ውላቸው ተጠናቆ የነበሩት እየሩሳሌም ታደሰ፣ ገነት ፈርዳ እና ማክዳ ዓሊ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ፊርማቸውን ያኖሩ ሦስት ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!