ሴቶች ፕሪምየር ሊግ| አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ውል አድሷል

አዳማ ከተማ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ እና የአማካዩዋን ውል አራዝሟል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን ዓመታት ሲጫወቱ የነበሩት አማካይዋ መቅደስ ማስረሻ እና ተከላካይዋ ትዝታ ገዛኸኝ የአዳማ አዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው፡፡

ከአዲስ ፈራሚዎቹ በተጨማሪ አማካይዋ አልፊያ ጃርሶ ውሏ ተራዝሟል፡፡ ደደቢትን ለቃ በ2011 አዳማ ከተማን መቀላቀል የቻለችው ተጫዋቿ በደደቢት ያሳካችውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ አዳማን በተቀላቀለችበት ዓመት ማሳካቷም ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ