የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታወቀ

የ2013 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ውድድር በታኅሣሥ ወር እንደሚጀመር ተገለፀ።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የሀገሪቱ ሦስተኛ የሊግ እርከን አንደኛ ሊግ የ2013 መርሀ ግብሩን በተመረጡ ሜዳዎች በስድስት ምድብ ተከፍሎ በሀምሳ አምስት ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

የዘንድሮው የአንደኛ ሊግ ውድድር በኅዳር ወር መጨረሻ ከአጠቃላይ ክለቦቹ ጋር ውይይት እና የዕጣ ማውጣቱ ሥነ ስርዓት ከተደረገ በኃላ ታህሳስ 11 ውድድሩ እንደሚጀመር ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በተያያዘ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ በአሁኑ ሰአት ክለቦች ምዝገባን እየፈፀሙ ሲሆን ለተጫዋቾች የዕድሜ ምርመራ (MRI) ከተደረገ በኃላ የሚጀመርበት ቀን ይፋ እንደሚሆን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!