በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው ሀድያ ሆሳዕና የ2013 ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት እንዲሁም ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፀሀፊ የነበሩትን እያሱ መርሀፅድቅን በረዳት አሰልጣኝነት የሾመው ሀድያ ሆሳዕና በክረምቱ ከሌሎች የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ቀደም ብሎ በርካታ ዝውውሮችን የፈፀመ ሲሆን እንደ በረከት ደስታ እና ምኞት ደበበን አይነት አዳዲስ ተጫዋቾችን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ መስጠቱም ይታወሳል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርም የሚጠበቀው ክለቡ በሆሳዕና ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ከጀመረ ሦስት ቀን አስቆጥሯል፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት በሆሳዕና እና አካባቢዋ ላሉ የክለቡ ተጫዋቾች የኮቪድ 19 ምርመራ ያደረገው ክለቡ ከሦስት ቀናት በፊት ደግሞ ከተለያዩ አካባቢዎች ለክለቡ ነባርም ሆነ አዲስ ሆነው ለመጡ ተጫዋቾች እና አጠቃላይ ለቡድኑ አባላት ተመሳሳይ ምርመራን ካደረገ በኃላ ውጤቱን መሠረት በማድረግ ማክሰኞ ለ2013 የወድድር ዘመን ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!