ምዓም አናብስት ድጋፍ አደረጉ

የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ለገበሬዎች ድጋፍ አድርገዋል።

ለቀጣይ ውድድር ዓመት በዝግጅት ላይ የሚገኙት መቐለዎች በዓድዋ ወረዳ ጣቢያ ደብረ-ገነት ለሚገኙ አርሶአደሮች የንዋይ እና የጉልበት ድጋፍ አድርገዋል። ይህ በክለቡ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ቡድን የተደረገው ድጋፍ ሰማንያ ሺሕ የሚያወጣ የማጭድ ድጋፍ ያጠቃለለ ሲሆን የክለቡ አባላትም በገበሬዎቹ ማሳ ተገኝተው በርካታ ሥራዎች እንደሰሩ ክለቡ አሳውቋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በማኅበረሰባዊ የበጎ ተግባራት ላይ ድጋፎች በማድረግ የሚገኙት መቐለዎች ከዚህ በፊት ለፍሬምናጦስ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በኮሮና ምክንያት ለተጎዱ በእንደርታ ወረዳ አከባቢ ለሚገኙ የማሕበረሰብ ክፍሎች እና ከተለያዩ አከባቢ ለተፈናቀሉ ወገኖች ጨዋታ አዘጋጅተው ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!