ዋልያዎቹ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሦስተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን በቀጣይ ሳምንት ያከናውናል።

ባለፈው ሳምንት ከዛምቢያ አቻው ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያከናወነው ብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾችን በመቀነስ ለኒጀሩ የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅቱን የቀጠለ ሲሆን ይበልጥ አቋሙን ለማወቅም በመጪው ዓርብ በ10:00 አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሦስተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታዉን እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!