በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ ተመራጭ ሠላሳ ተጫዋቾቹን አሳውቋል።
ከህዳር 22-ታኅሣሥ 6 በታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚደረገው ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነውና ከኬንያ እና ሱዳን ጋር የተደለደው ቡድኑ በዛሬው ዕለት ለሠላሳ ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል። ይህን ተከትሎም ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት የኮቪድ ምርመራ ያካሄዱ ሲሆን ማረፊያቸውንም ብሉ ስካይ ሆቴል በማድረግ ከኮቪድ ውጤት በኋላ ልምምዳቸውን የሚጀምሩ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር
ግብጠባቂዎች
ለይኩን ነጋሽ (ሲዳማ ቡና)፣ ታሪኩ አረዳ (መከላከያ)፣ ዳግም ተፈራ (ሀዋሳ ከተማ)
ተከላካዮች
ኃይለየሱስ ይታየው (ባሕር ዳር ከተማ)፣ ኃይለሚካኤል አደፍርስ (ሰበታ ከተማ)፣
ዳዊት ወርቁ (ወልዋሎ)፣ ክፍሌ ኪአ (ሲዳማ ቡና)፣ አማኑኤል እንዳለ (ሲዳማ ቡና)፣ ወንድማገኝ ማዕረግ (ሀዋሳ ከነማ)፣ ፀጋአብ ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዘነበ ከድር (ሀዋሳ ከተማ) ቴዎድሮስ ብርሀኑ (ወልቂጤ ከተማ)
አማካዮች
ጌታ ሰጠኝ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ አበባየሁ ሀጪሶ (ወላይታ ድቻ) አቤል እያዩ (ፋሲል ከነማ)፣ ተመስገን በጅሮንድ (ሲዳማ ቡና)፣ ወንድማገኝ ኃይሌ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ቢኒያም ካሣሁን (አርባምንጭ ከተማ)፣ ሲራክ ቶፌ (አርባምንጭ ከተማ)፣ አማኑኤል ተረፈ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ብሩክ ኤልያስ (ደቡብ ፖሊስ)
አጥቂዎች
ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ (ፋሲል ከነማ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)፣ ተመስገን በጅሮንድ(ሲዳማ ቡና)፣ ሠመረ ሀፍተይ (ወልዋሎ አዲግራት)፣ በየነ ባንጃ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ እዮብ ማቲዮስ (አዳማ ከተማ)፣ እያሱ ለገሰ (አዲስ አበባ ከተማ)፣ ተባረክ ኢፋሞ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ቤዛ መድህን (ኢኮሥኮ)
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!