ከፍተኛ ሊግ| ጌድኦ ዲላ አዲስ ፕሬዝዳንት ሲሾም የተጫዋቾችን ቅሬታ ለመመለስ እየሠራ እንደሆነ ተገለፀ

ጌዴኦ ዲላዎች አዲስ ፕሬዝዳንት ሲሾሙ ለተጫዋቾቻቸው ቅሬታ ምላሽ ለመስጠትም እየሠሩ እንደሆነ ተገልጿል።

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ የሚወዳደሩት ጌዴኦ ዲላዎች ባለፉት ዓመታት በክለቡ በተለያዩ የኃላፊነት ሥራዎች ላይ የሰራው ተዘራ ጌታሁንን በፕሬዝዳንትነት ሾመዋል። ከዚህ በፊት በክለቡ በስራ አስከያጅነት በቆዩባቸው ጊዜያት በርካታ ሥራዎች የሠሩት አዲሱ ፕሬዝዳንት በቀጣይም ክለቡን አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንደሚሠሩ፣ ክለቡ በወጣቶች እና በአከባቢው ታዳጊዎች የተገነባ የህዝብ ቡድን ለማድረግ እንደሚሰሩ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና ባለፈው ዓመት ክለቡን ያገለገሉት ተጫዋቾች ከደሞዝ ጋር የተያያዘ ያቀረቡትን ጥያቄ ለመመለስ ክለቡ እየሠራ እንደሚገኝና በጥቂት ጊዜ ውስጥ ጥያቄያቸው እንደሚመለስ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!