የፕሪምየር ሊጉ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት የሚደረግበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት በቀጣይ ሳምንት ይደረጋል።

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታኅሣሥ 3 በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚደረጉ ጨዋታዎች በይፋ ይጀመራል፡፡ የዚህ ውድድር የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ ኅዳር 5 ከቀኑ 8:00 በአዲስ አበባ እንደሚወጣም የኩባንያው የፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

አቶ ክፍሌ “ቀደም ብለን ለማውጣት አቅደን የነበረበት ሆቴል በመያዙ ሌላ አማራጭ ቦታ ለፕሮግራሙ እየፈለግን ነው።” ሲሉ የገለፁ ሲሆን ተለዋጭ ቦታውንም የፊታችን ሰኞ ለክለቦች በደብዳቤ ገልፀው እንደሚልኩ አክለው ነግረውናል፡፡ ይህ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት በዲኤስ ቲቪ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!