ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የበርካታ ወሳኝ ተጫዋቾችን ዝውውር ቀደም ብሎ የፈፀመው መከላከያ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ በ2013 ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን አዲስ አሰልጣኝ ከሾመ በኋላ ወሳኝ ተጫዋቾችን በማስፈረም ተጠምዶ የነበረው መከላከያ ሁለት ወጣት ጫዋቾችን ወደ ክለቡ ስብስብ ካካተተ በኃላ ዝውውሩን ፈፅሞ ወደ ቅደመ ውድድር ዝግጅት ገብቷል፡፡

ተስፈኛዋ አጥቂ ህዳት ካሡ ክለቡን የተቀላቀለች ተጫዋች ነች። በሁለተኛ ዲቪዚዮኑ ክለብ ቦሌ ክፍለ ከተማ ስትጫወት የቆየችው ህዳት በተሰረዘው የ2012 የሁለተኛ ዲቪዝዮን ውድድር ላይ በዘጠኝ ጎሎች የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን ስትመራ የነበረ ሲሆን በቅርቡ ክለቡን ከተቀላቀለችው ሴናፍ ዋቁማ ጌር ጥሩ ጥምረት ትፈጥራለች ተብሎ ይጠበቃል።

ሌላኛዋ የክለቡ ፈራሚ መዲና ጀማል ነች። በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን በአማካይ ስፍራ ስታሳይ የነበረችው መዲና ከዚህ ቀደም ለጥረት እንዲሁም በተሰረዘው የውድድር ዓመት ደግሞ በአዲስአበባ ከተማ ተጫውታ አሳልፋለች።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ