መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል

ኢትዮጵያን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚወክሉት መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ  የቅድመ ማጣርያ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።

የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንድርታ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር ሲደለደል ይህን ዙር የሚያልፍ ከሆነ በአንደኛ ዙር የቱኒዚያው ጠንካራ ክለብ ኤስፔራንስ ደ ቱኒስን የሚገጥም ይሆናል።

በዛው ዓመት የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊው ፋሲል ከነማ ከቱኒዚያው ዩ ኤስ ሞናስቲር ጋር መደልደሉ ታውቋል። ይህን ዙር የሚያልፍ ከሆነም ከሊቢያው አህሊ ትሪፖሊ ጋር የሚጫወት ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ