ኢትዮጵያ ቡና ለባለውለታዎቹ የዕውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከምስረታው ከ1968 – 2013 በዕውቀታቸው በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እስካሁን እገዛ ላደረጉ የክለቡ ባለውለታዎች የዕውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ትናንት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ማካሄዱን ገልጿል።

ከኢትዮጵያ ቡና ያገኘነው መረጃ ይህን ይመስላል:-👇

“በዕለቱ ለክለቡ እና ለደጋፊ ማኅበሩ ግልጋሎት የሰጡ ከመንግስት እንዲሁም ከስፖርቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው የክብር እንግዶች፣ የክለባችን አሰልጣኞች እና ሙሉ ተጫዋቾች፣ የክለባችን ደጋፊዎች በተገኙበት ነበር።

“ክቡር የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የበላይ ጠባቂ ለመሆን መስማማታቸውን በመግለጽ ፤ በቦታው በተገኙት የዶክተር ሙላቱ ተወካይ የመክፈቻ ንግግር ፕሮግራሙ ተጀምሮዋል።

“በቀጣይም የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ጀምሮ ይህንን ፕሮግራም በዋና ኮሚቴነት የመሩእና እየመሩ ያሉ፣ በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና ደጋፊዎች ማህበርን የመሩ፣ ገንዘባቸውንና ዕውቀታቸውን የሰጡ፣ በCovid-19 ወቅት ደሞዛቸውን የቀነሱ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾችእና የፅ/ቤት ሰራተኞች፣ በካምፕ ግንባታው ላይ ገንዘባቸውን በማውጣት የተጫዋቾች ቤት ለሰሩ ባለውለታዎች የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

“በኢትዮጵያ ቡና የ45 ዓመት ጉዞ ውስጥ የራሳቸውን ትልቅ አሻራ አኑረዋል ለተባሉ አካላት ልዩ ዕውቅና እና ክብር ተሰጥቷቸዋል።

ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ተጫውተው ላለፉ ተጫዋቾች-

፩ አሸናፊ በጋሻው
፪ አሰግድ ተስፋዬ
፫ ተሾመ ተፈራ (ተሼ ብረቱ) እና
፬ ተስፋዬ ጅማ በልዩ ሁኔታ ለእያንዳንዳቸው የአንድ መቶ ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

“ኢንተር ኮንትኔታል የተደረገውን ዝግጅት አጋራችን የሐበሻ ቢራ አ.ማ ድጋፍ ስላደረግልን ከልብ እናመሰግናለን።”

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!