አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ | ወደ ኒጀር የሚጓዙ 23 ተጫዋቾች ይፋ ሆነዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ የምድብ ማጣርያ ከኒጀር ጋር ኒያሜ ላይ ይጫወታል። ወደ ስፍራዎ የሚጓዙ 23 ተጫዋቾችም ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በስብስባቸው ከነበሩት 26 ተጫዋቾች መካከል ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ አማካዩ ሀብታሙ ተከስተ እና ጉዳት ላይ የሚገኘው ሙጂብ ቃሲም አብረው የማይጓዙ ሲሆን አሰልጣኙ ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ ባስታወቁት መሰረት ሦስቱ ተጫዋቾች አዲስ አበባ ቆይተው ቡድኑ ከኒያሜ ሲመለስ ስብስቡን መልሰው የሚቀላቀሉ ይሆናል።

ወደ ኒያሜ የሚያመሩት 23 ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች

ምንተስኖት አሎ፣ ጀማል ጣሰው፣ ተክለማርያም ሻንቆ

ተከላካዮች

አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባየህ፣ ወንድሜነህ ደረጀ ፣ መሳይ ጳውሎስ፣ ረመዳን የሱፍ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሱሌይማን ሀሚድ፣ ሽመክት ጉግሳ 

አማካዮች

ሽመልስ በቀለ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ይሁን እንደሻው፣ ታፈሰ ሰለሞን፣ መስዑድ መሀመድ፣ አማኑኤል ዮሐንስ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ሀይደር ሸረፋ

አጥቂዎች

ጋዲሳ መብራቴ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ አቡበከር ናስር፣ ጌታነህ ከበደ

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!