ኢትዮጵያውያን ዳኞች ወደ ሞዛምቢክ ያመራሉ

ኢትዮጵያውያን ዳኞች ለሞዛምቢክ እና ካሜሩን ጨዋታ በካፍ ተመድበዋል።

የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ እና አራተኛ የማጣርያ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት መጨረሻ መደረግ የሚጀምሩ ሲሆን ማፑቱ ላይ የውድድሩ አዘጋጅ ካሜሩን ከምድቡ መሪ ሞዛምቢክ በቀጣይ ሳምንት ሰኞ የምታደርገው አራተኛ ጨዋታን እንዲመሩ ካፍ በቅድሚያ አራት የሲሸልስ ዳኞችን መርጦ የነበረ ቢሆንም ሁለቱን በኢትዮጵያውያን ተክቷል። በዚህም መሠረት በረዳትነት ፋሲካ የኋላሸት፣ በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ቴዎድሮስ ምትኩ እንዲመሩ ተመድበዋል። ሲሸልሳዊያኑ በርናርድ ካሚሌ (ዋና) እና ዳኒ ፔትሮሴ (ረዳት) ሌሎች አብረው የሚዳኙ ዳኞች ናቸው።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!