ከፍተኛ ሊግ | መከላከያ አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም በርካታ ወጣቶችን አሳድጓል

መከላከያዎች አንድ ተጫዋቾች ሲያስፈርሙ ሰባት ታዳጊ ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል፡፡

ወሳኝ ዝውውሮች የፈፀመው የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌው መከላከያ ከሌሎች የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ቀደም ብሎ በቢሾፍቱ አየር ኃይል ሜዳ ዝግጅቱን የጀመረ ቢሆንም ከወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታዎች አንፃር ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በክረምቱ አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የነበረው መከላከያ የመጨረሻ ተጫዋች በማድረግ የቀድሞው የመድን ሰበታ እና አውሥዶድ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ሲጫወት የነበረው ኤርሚያስ ፍሰሀን አዲስ ተጫዋች አድርጎ አስፈርሟል፡፡

ቡድኑ ከአዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ ከታችኛዎቹ ከ17 እና ከ20 ዓመት ቡድኑ ስልሳ ተጫዋቾችን በጨዋታ ከተመለከተ በኃላ ሰባት ተጫዋቾችን አሳድጓል፡፡ ዓዲስአለም አማረ፣ ድልአዲስ ገብሬ፣ ዮናስ ለገሰ፣ ኤልያስ እንደሻው ፣ ናትናኤል ሰለሞን፣ ዮዳሄ ዳዊት እና ፈይሣ አዳሙ ወደ ዋናው ቡድኑ ያደጉ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!