አዳማ ከተማ ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በዚህ ሳምንት ይጀምራል

አዳማ ከተማዎች 2013 የውድድር ዓመት ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል፡፡

ካለፉት ዓመታት በተለየ መልኩ ከከፍተኛ ሊጉ እንዲሁም ጥቂት ተጫዋቾችን ከፕሪምየር ሊጉ ያስፈረመው አዳማ ከተማ ከፈረሙ ተጫዋቾች ባሻገር አብዛኛዎቹን በሙከራ ከተመለከተ በኃላ የመጨረሻ ፈራሚዎቹን ከሰሞኑ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል እና ረዳቶቹ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በዛሬው ዕለት ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቦ ሁሉም ወደ ካምፕ ገብተዋል፡፡

ነገ (ረቡዕ) ለሁሉም አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች እና ለክለቡ አባለት የኮቪድ 19 ምርመራን ካደረጉ በኃላ ውጤቱን መሠረት በማድረግ የፊታችን ዓርብ ወደ ዝግጅት እንደሚገቡ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ዝግጅታቸውን በሌላ ከተማ ለማድረግ አቅደው የነበረ ቢሆንም ከወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየሰሩ ይቀጥላሉ፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!