የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አዲስ ውሳኔ ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል።
አንድ ዓመት የሞላው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከደቂቃዎች በፊት የ2013 ውድድር የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በካፒታል ሆቴል እና ስፓ አከናውኗል። የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓቱ ከቀጥር በኋላ ከመደረጉ በፊትም ማኅበሩ ክለቦችን ዝግ በሆነ ስብሰባ በማስቀመጥ አወያይቷል። በስብሰባውም የማኅበሩ አባላት (ክለቦች) አንድ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሰረት ሁሉም የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የሴት ቡድን እንዲኖራቸው ተወስኗል። ክለቦቹ ከሴት ቡድን በተጨማሪ ከ23፣ ከ17 እና ከ15 ዓመት በታች ቡድኖቸን አቅፈው ውድድር እንዲያደርጉ ውሳኔ ተላልፏል። በተጨማሪም ክለቦች ከ20 ዓመት በታች ውድድር እንዲቀር መወሰናቸው የተገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ዙርያ ኩባንያው ከፌዴሬሽኑ ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሏል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!