ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ጌዲኦ ዲላ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም በርካታ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል

ጌዲኦ ዲላ የአሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካን ውል ሲያራዝም ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ጨምሮ አስራ አራት ነባሮችንም ለተጨማሪ አመት አስፈርሟል፡፡

የክለቡ አዲስ ፈራሚዎች:- መስከረም መንግሥቱ (ግብ ጠባቂ ከአዳማ ከተማ)፣ ገሊላ አበራ (ግራ ተከላካይ ሀዋሳ ከተማ)፣ ደመቀች ዳልጋ (ተከላካይ ከንግድ ባንክ)፣ በላይነሽ ልንገርህ (ተከላካይ ከቂርቆስ)፣ ይታገሱ ተገኝወርቅ (አጥቂ ሀዋሳ ከተማ)፣ ወርቅነሽ መሰለ (አማካይ ሀዋሳ ከተማ)፣ ቱሪስት ለማ (አጥቂ ከአርባምንጭ ከተማ)፣ ሰላማዊት ጎሳዬ (አጥቂ ከአቃቂ)፣ ሳባ ኃይለሚካኤል (አጥቂ ከንግድ ባንክ) አዳዲስ የክለቡ ፈራሚዎች ሆነዋል፡፡

ከአዳዲሶቹ ተጫዋቾች በተጨማሪ ስመኝ ምህረቴ፣ ቤተልሄም አስረሳኸኝ፣ እፀገነት ግርማ፣ መንደሪን ክንዲውን እና ሌሎች ተጨማሪ አስር በድምሩ አስራ አራት ተጫዋቾች በክለቡ ውል አድሰዋል፡፡ ክለቡ የኮቪድ 19 ምርመራን ካደረገ በኃላ ወደ ልምምድ ከገባ ሳምንት አልፎታል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!