ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈረመ

አቃቂ ቃሊቲ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ ሁለት ታዳጊዎቸችን አሳድጓል፡፡

አሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳን ከቀጠሩ በኃላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከቀናት በፊት አስፈርመው ከነባሮቹ ጋር አዋህደው ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የገቡት የአቃቂ ቃሊቲዎች ተጨማሪ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ሔለን ሙሉጌታ (ግብ ጠባቂ ከፋሲል ከነማ)፣ ያብስራ ይታይህ (አጥቂ ከፋሲል ከነማ)፣ የትምወርቅ አሸናፊ (አጥቂ ከአርባምንጭ) አዳዲስ ፈራሚዎቹ ሲሆኑ ሩት ሚልዮን (ተከላካይ) እና ፍሬህይወት ኩማ (አማካይ) ከታዳጊ ቡድን ያደጉ ተጫዋቾች ሲሆን አጥቂዋ ሔለን መሰለ ደግሞ ውሏ መራዘሙን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!