ሀዋሳ ከተማ የጋናዊውን ተከላካይ ውል አራዘመ

ላውረንስ ላርቴ ለተጨማሪ ዓመት በሀዋሳ የሚያቆየውን ውል አራዘመ፡፡

በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረት መሪነት ልምምዳቸውን ከጀመሩ ሳምንታት ያለፋቸው ሀዋሳ ከተማዎች አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን 2009 ክለቡን የተቀላቀለውን ጋናዊውን የመሐል ተከላካይ ላውረንስ ላርቴን ለተጨማሪ አንድ ዓመት አስፈርሟል፡፡

ይህ የቀድሞው የአያክስ ኬፕታውን እና ክለብ አፍሪካን ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ መቶ ሀዋሳ ከተማን ከተቀላቀለ በኃላ ያለፉትን አራት ዓመታት ለሀዋሳ የመከላከል ጥንካሬን በመስጠት ተጠቃሽ ሲሆን አሁንም በክለቡ መፈረሙ የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱን ቡድን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!