ክልሎች ለ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መልምለው እንዲልኩ ጥሪ ቀረበ

በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ለሚደረገው ውድድር ይመጥናሉ የሚሉትን ተጫዋቾች መልምለው እንዲልኩ ፌዴሬሽኑ ለክልሎች ጥሪ አቀረበ፡፡

የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ከታህሳስ 13 እስከ 28 በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ይደረጋል፡፡ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ እና ኬንያ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንድሪያስ ብርሀኑን ከሁለት ሳምንት በፊት በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን ለብሔራዊ ቡድኑ በፍጥነት የሚመጥኑ ተጫዋቾችን ለመመልመል ሲረዳው የቆየው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ከሁለት ዓመታት በፊት በመቋረጡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አማራጭ ብሎ ተጫዋቾችን ለማግኘት ለአስሩ ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ደብዳቤ የላከ ሲሆኑ ሁሉም ክልሎች እስከ ኅዳር አምስት ለብሔራዊ ቡድኑ ይመጥናሉ የሚሉትኝን ሦስት ሦስት ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾችን እንዲልኩ ጠይቋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ