ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ ዱራሜ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

ሀምበሪቾ ዱራሜ የከፍተኛ ሊግ ልምድ ያለው አሰልጣኝ ሹሟል፡፡ 

በተሰረዘው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ዓለማየሁ አባይነህ ሲመራ ቆይቶ በዓመቱ አጋማሽ ከአሰልጣኙ ጋር የተለያየው ሀምበሪቾ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ካፈላለገ በኃላ አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ (መንቾን) በአንድ ዓመት የውል ዕድሜ አሰልጣኙ አድርጎ ቀጥሯል፡፡

ሀድያ ሆሳዕናን በ2007 እንዲሁም ዓምና በ2011 ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሁለት ጊዜ ማደግ እንዲችል ያደረጉት አሰልጣኙ በ2010 ደቡብ ፖሊስንም ከከፍተኛ ሊጉ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኃላ ዳግም ፕሪምየር ሊጉን ሲቀላቀል አሰልጣኙ ቡድኑን እየመሩ በማስገባቱ ረገድ ድርሻቸው ላቅ ያለ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ሀድያ ሆሳዕናን በፕሪምየር ሊጉ እየመሩ አመቱን ቢጀምሩም ከውጤት ጋር በተገናኘ ለመለያየት የተገደዱት አሰልጣኙ ክለቡን ለቀው ኢትዮጵያ መድንን መያዝ ቢችሉም ሊጉ በኮቪድ 19 በመቋረጡ ውላቸውን አንድም ጨዋታ ቡድኑን ሳይመሩ በስምምነት ተለያይተው ወደ ሀምበሪቾ አምርተዋል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ