ብሔራዊ ቡድኑ የሚጫወትበት ሜዳ ጉዳይ ?

የብሔራዊ ቡድኑ የማክሰኞውን የማጣርያ ጨዋታ ባህር ዳር ላይ ያደርግ ይሆን?

በ2021 ለሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታውን ወደ ኒያሚ አቅንቶ ሽንፈት አስተናግዶ የተመለሰው ብሔራዊ ቡድናችን ማክሰኞ ሌላኛውን አራተኛ የምድብ ጨዋታውን ባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚያደርግ አስቀድሞ መርሐግብር መውጣቱ ይታወቃል።

ዋልያዎቹ በዚህ ሰዓት የአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት እና ዋናው ፀሀፊ በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ነገ ወደ ባህርዳር እንደሚጓዙ መረጃዎች እየወጡ ቢሆንም ይህን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር የማክሰኞ ጨዋታ ወደ ሌላ ስታዲየም ለማዞር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ለመገንዘብ ችላናል።

የፌዴሬሽኑ አመራሮች ከሚመለከተው የመንግስት አካላት እና የካፍ አመራሮች ጋር ንግግር እያደረጉ ሲሆን ነገ ጨዋታው የሚደረግበት ቦታን ፌዴሬሽኑ ለሚዲያ አካላት ይፋ እንደሚያደርግ ለማወቅ ችለናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!